በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በአልማዝ አያና የወርቅ በጥሩነሽ ዲባባ የብር ሜዳልያ አገኘች

0
32
Spread the love

በለንደን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አገኘች፡፡

አልማዝ እንደተለመደው ከተወሰኑ ዙሮች በኋላ ተስፈንጥራ ወጥታ ቀሪዎች ዙሮች ብቸዋን በመሮጥ ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቅ ችላላች፡፡

አልማዝ ርቀቱን 30:16.32 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለችው፡፡

ጥሩነሽ ዲባባ ከኬንያዉያን የገጠማትን ብርቱ ፍኩክር በመቋቋም ከአልማዝ ተከትላ ሁለተኛ መውጣት ችላለች፡፡ ጥሩነሽ 31:02.69 በማስመዝገብ ነው የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች፡፡

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ ተወዳዳሪ ዴራ ዲዳ 14ተኛ ወጥታለች፡፡

በውድድሩ ኬንያዊቷ አጀንስ ጂቤት 31:03.50 በሆነ ሰዓት 3ተኛ ደረጃን በመያዝ የነሃስ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች፡፡