ኢትዮጵያ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ወደ ውጭ በመላክ 44 ሚሊዮን ዶላር አገኘች

0
110

ኢቢሲ ሐምሌ 27፤2009

ኢትዮጵያ ከተንቀሳቃሽ ስልኮችና መለዋወጫዎቻቸው 44 ነጥብ 14 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ተስፋዬ ለኢቢሲ እንደተናገሩት የውጭ ምንዛሪው የተገኘው ምርቶችን ወደ አውሮፓና አፍሪካ አገራት በመላክ ነው፡፡

የዘርፉ አፈጻጸም 73 ነጥብ 57 በመቶ መሆኑን አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

በበጀት አመቱ ከዘርፉ 60 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 44 ነጥብ 14 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል፡፡

በዘርፉ የተገኘው ገቢ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ3 ዕጥፍ አድጓል ተብሏል፡፡

በ2008 ዓ.ም ከዘርፉ የተገኘው ገቢ 15 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡

በአብዱልአዚዝ የሱፍ ኢቢሲ

Spread the love