የህዳሴ ግድብ ግንባታ 60 በመቶው ተጠናቀቀ

0
315

ነሃሴ 02፤ 2009 ኤዜአ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አጠቃላይ አፈፃፀም 60 በመቶ መድረሱ ተገለጸ።

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የግድቡን የሲቪል፤ የሃይድሮ እና ኤሌክትሮ መካኒካል የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

የግድቡ የሲቪልና መካኒካል ስራ በክረምት ወቅትም እንደነበረው ለማስቀጠል የጎርፉን ሁኔታ አስቀድሞ በመገንዘብ በጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ወደ ቅድመ ኃይል ማመንጨት ለመግባት ስራው በተፋጠነ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን ነው ዶክተር ደብረፅዮን የተናገሩት፡፡

በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ግድቡ ኃይል ማመንጨት እንዲጀምር ለማድረግ መታቀዱን አዜአ ዘግቧል፡፡

ምንጭ፡ ኤዜአ

Spread the love