የሰበታ ከተማ ከንቲባ የነበሩትን ጨምሮ በሙስና የተጠረጠሩ 26 ግለሰቦች ተያዙ

0
346

 

የሰበታ ከተማ ከንቲባ የነበሩትን ጨምሮ በሙስና የተጠረጠሩ 26 ግለሰቦች ተያዙ
Tue, Aug 08, 2017 በሪሁ ሽፈራው ዜና

የሰበታ ከተማ ከንቲባ የነበሩትን ጨምሮ በሙስና የተጠረጠሩ 26 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኦሮሚያ የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ ።

የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት፤መሀንዲሶች፣ የቢሮ ሰራተኞች እና ደላሎችም በቁጥጥር ስር ከዋሉት 26 የሙስና ተጠርጣሪዎች ውስጥ ናቸው ፡፡

ከተጠርጣሪዎችም በሰበታ ከተማ አስተዳደር በከንቲባነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ገዛኸኝ ጎቤ እንደሚገኙበት ኃላፊው አስታውቀዋል ።

ግለሰቦቹ በሰበታ ከተማ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የተመደበ ሀብትን በመመዝበር፣ የሀሰት የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ እና ደረሰኝ በማዘጋጀት በመስጠት የተጠረጠሩ ናቸው።

በተጨማሪም የይዞታ ማረጋገጫ እና ሀሰተኛ ደረሰኝ በመስጠት እና በመሸጥ፣ የካሳ ክፍያ ለማይገባቸው ክፍያ በመፈፀም እና መቀበልም ተጠርጥረዋል ሲሉ አስረድተዋል ።

ተጠርጣሪዎቹ በአነስተኛ እና ጥቃቅን በሀሰት በመደራጀት ገንዘብ በመውሰድም ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት ብለዋል ፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

Spread the love