የአሜሪካ ኤምባሲ በኮምፒዩተር ፕሮግራሚንግ ያሰለጠናቸውን የ11ኛ ክፍል ሴት ተማሪዎችን አስመረቀ

0
321

ነሃሴ 02፤ 2009

ገርልስ ካን ኮድ ፕሮጀክት ከአዲስ አበባ ከሚገኙ ከ10 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የ11ኛ ክፍል ሴት ተማሪዎችን በኮምፒዩተር ኮዲንግና ፕሮግራሚንግ ተመርቀዋል፡፡

ስልጠናው የተቀረጸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ  መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በባህዳር፤ መቀሌና ጅማን ጨምሮ በአጠቃላይ አምስት ከተሞች ስልጠናው ለ200 ሴት ተማሪዎች እንደተሰጠ ተገልጿል፡፡

የስልጠናው ዋና አላማ በተማሪዎች ዘንድ አብዛኛውን ጊዜ የማይደፈሩትን የሳይንስ ትምህርት ዘርፎችን በተለይም የኮምፕዩተር እውቀትን በተሻለ ሁኔታ ለማስጨበጥና የሴቶችን በራስ የመተማመን መንፈስን ለማጠናከር ነው ተብሏል፡፡

በናትናኤል ጸጋዬ

Spread the love