በ2016 VOA Amharic ቃለ መጠይቃቸውን ሆን ተብሎ የተቆራረጠውና የተጭበረበረው አሁን ግልጽ ሆኖ ወጣ።የአዋሳ ከተማ መስራችና የቀድሞ የትግራይ ገዢ ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም ዛሬ ከDW ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ የራያና የወልቃይት ታሪካዊ ባለቤትነት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

0
9403

የልኡል ራስ መንገሻ ስዩም የህይወት ታሪክ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።
በ2016 VOA Amharic [Interview – Prince Mengesha Seyoum] ቃለ መጠይቃቸውን ሆን ተብሎ የተጭበረበረ ማለትም ኤድትድ የተደረገው የድምጽ ኢንተርቪው መቅረቡ ይታወሳል። በVOA Tigrigna ላይ ግን ያልተቆርረጠ ሃሳባቸው ተላልፎ ነበር። በአማርኛው ላይ እሳቸው እንዳሉት በሳቸው ግዜ ወልቃይት በቤጌ ምድር ይተዳደር እንደነበር ተጠይቀው እንደመለሱ። ከዛ ውጪ ግን በአባታቸው ዘመን ይሁን ከዛ በፊት ግን ወልቃይትና አከባቢው የትግራይ ክልል ስልጣን ስር ይተዳደር እንደ ነበር ና በጃንሆይ ትእዛዝ ከትግራይ ተነጥቆ ወደ ቤጌ ምድር አስተዳደር እንደተወሰደ እንዳይታወቅ ለማድበስበስ ተምታቶ መቅረቡን በትግርኛው ላይ በተቃውሞ በዚያን ጊዜ መናገራቸው በሰፊው ተዘግቦ ነበር። ይህም ይህም እባባዊ የተንኮል ሴራ ወንድማማች የሆኑትን ያማራና የትግራይ ህዝቦችን ለማዋጋት ባይሳካላቸውም ለጊዜዊ ፕሮፖጋንዳ በሰፊው ሊጠቀሙበት ጥረዋል። ይህንን ለማረጋገጥ አሁን በግልጽ በቪድዮ ማን ይናገር የነበረ – ማን ያርዳ የቀበረ  እንዲሉ በህይወት ካሉ የቀዳማዊ ሃይለስላሴ የመጨረሻው ራስ አዛውንቱ ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም ዛሬ ከDW ባደረጉት ቃል ምልልስ ስለ ራያና ወልቃይት ታሪካዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። እንደ ልኡል ራስ መንገሻ ስዮም ማብራሪያ ወልቃይት ፀገዴና ራያ እሰከ አልውሃ ምላሽ ድረስ እስከ 1948 ዓ/ም በትግራይ መስተዳደር ስር እንደነበሩና ከዚያ በኋላ ከንጉስ ሃይለስላሴ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ወልቃይት ፀገዴ እና አካባቢው በጎንደር እንዲሁም ደቡባዊው የራያ አካባቢ ማለትም ቆቦ አላማጣና ኮረም በወሎ ክፍለሃገር ሰር ሁነው እንዲተዳደሩ ተደረገዋል ብለዋል።

Interview-Prince-Mengesha-Seyoum-2016 Tigrigna VOA (2016 Interview – Prince Mengesha Seyoum)
Facebook Comments Box
Spread the love