ከታሪክ ማህደር እይታ፤ ዶ/ር አብይ ወደ አባ ገነንነት እያኮበከቡ ይሆን?

0
810

ዶ/ር አብይ ወደ አባ ገነንነት እያኮበከቡ ይሆን? የፊደራል ኅይሎች የአመራር አባላት በዶ/ር አብይ አመራር ታፊኑ ሲል የትግራይ ቲቪ እና የታመኑ ምንጮች ጭምር አስታውቀዋል። ነገሩ በአገራችን ከኢሀዲግ ዘመን በባሰ ዲሞክራሲ ይባስ ጫጭታለች ወደ ማለት ሊያመጣን ነው። ተስፉ የተደረገባቸው ዶ/ር አብይ ወደ አምባ ገነንነት እያኮበከቡ ነው። ባይሆን ኖሮ በበታች ባለስልጣኖች በትግራይ ተወላጆ ላይ በስውር የሚካሄዱ አፈናዎች እና አንድ በአንድ የማጥቃት ዘመቻ፣ ምርጥ ምርጥ የቤት ኪራይ የያዙ ግለ ሰቦችን በውሸት ውንጀሎ ቤት መንጠቅን፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክንያት ኢትዮጵያን ቀላል ኢላማ ለማድረግ ኤርትራ ለግብፅ የጦር ሰፈር መፍቀድን ወዘተ… ያወግዙ ነበር ዝም ማለታቸውና ተው እንደማለት ኢሳያስን አቅፎ መሳማቸው አሸሼ፟ገዳም ማለት መብዛቱ ግን ተባባሪ ያደረጋቸው ይመስላል። ይህ አካሄድ ልክ በኤርትራ ህዝብ ላይ በታሪክ በማእከላዊ መንግስት የተካሄደው ሴራ ኤርትራን እንድትገነጠል እንዳነሳሳ ትግራይንም አብዝቶ መግፋቱ ለዚህ አላማ መሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥተዋል። የኤርትራን የመገንጠል ታሪክ ጅማሪ ስናይ። ከአድዋ ጦርነት ድል ቡሀላ ኢትዮጵያን ከውጭ ወራሪዎች ለመታደግ ከ17 ጦርነት በላይ ተዋግተው ድል የነሱት ራስ አሉላ ከኢትዮጵያ ብዙ አርበኞች መካከል የአድዋ ድል ዋንኛ ተዋጊ የመጀመሪያውን የቆረጣ ውጊያ በጣሊያን ላይ የጀመሩ እንደነበሩ የታወቀ ነው። ራስ አሉላ በወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ አፄ የሚኒልክን ከአድዋ ድል ቡሃላ ኤርትራን ጭምር ከጣሊያን ነፃ እናውጣ ቢልዋቸው ንጉሡ ስንቅ አልቆብናል ብለው እምቢ አሉ። እንዳውም መረብ ምላሽ ለጣሊያኖች ፈርመው ሰጡ በምላሹ ጥቂት መሳሪያዎች እና ወርቅ ተቀብለው ሽጥዋቸው። ከዛን ጊዜ ቡሀላ ጣሊያን 70 አመት ኤርትራን ረግጦ ገዛ የግፉ ብዛት ባንደ ከሆኑት በቀር ተቃዋሚዋችን ገድሎ በባሪላና በጋሪ የቆሻሻ ገንዳ ላይ ይጥላቸው ነበር። በመጨርሻ ጃንሆይ አፄ ሀይለስላሴ በፊደረሽን ማለትም በራስ ገዝ ተስማምተው የተባበሩት መንግስታት ከእንግሊዝ ጋር አብሮ ለኢትዮጵያ ተመለሰች። ህዝቡም ምኒልክ ሸጡን ከሚለው ቁጣ በርዶ በደስታ ተዋሀደ ነበር ሆኖም ከጥቂት አመት ቡሀላ ራስ ገዝ መሆንዋን ጥሰው ፋብሪካዋችን እየነቀሉ ወደ መሀል መውሰድ እራስ ገዝ እንዳትሆን ሹመኞችን ከመሀል መሾም ወዘተ ጀመሩ ህዝቡም ለመገንጠል አመፀ መጀመሪያ እስላሞቹ ጀብሀ ተነሳ ያንን ለመዋጋት ኢሳያስን ጃንሆይ አስታጥቀው የአሁኑ ሻቢያን አዘመቱ። በመሀል ደርግ ስልጣን ሲይዝ ኢሳያስ በዛው የጎበዝ አለቃ ሆኖ ሸፈተ። ደርግም ተገንጣይ ሁላ እያለ የእርጉዝ እናቶች ሆዳቸውን መቅደድ ወጣት አዛውንት መረሸን አበዛ ህዝቡም ተሰደደ አውሬ እንዲሆኑ ተገደዱ በትግልም ነፃ ወጡ። አሁንም በወያኔ ሰበብ የትግራይ ህዝብ ላይ ዘዲያዊ ማሳቀቅ ማሸማቀቅ ሲካሄድ ዶክተር አብይ መፍቀዳቸው ትግራይ ሌላ አማራጭ እንድታይ ለማስገደድ ይመስላል። ትግራይ ብትገነጠል በታሪክ ተጠያቂው ወያኔ ብቻ ሳይሆን ዋናው ዶ/ር አብይ ናቸው እሳቱን ሰባት እጥፍ ማንደድ ለማንም አይጠቅም። ገብስ ሲያረጅ አባቱን ይመስላል እንዳሉ ትግራይ ላይ ላለፉት 2 አመታት መንገድ ከመዝጋት ልጀምሮ ልዩ ልዩ ተፅህኖ እና ማግለል መቆም አለበት። ትግራይ የኢትዮጵያ ናት ኢትዮጵያም የትግራይ ናት። በስልጣን ሽኩቻ ኢትዮጵያን አትበትንቡን ሁላችሁም አደብ ግዙና ተወያዩ ተስማሙም። ትግራይ መርዋት የሀይል ምላሽ መስጠት ከጀመረች አደጋው ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለማእከላዊ መንግስት ህልውና ጭምር መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ትግራይ የሱማሌ ክልል ወይም ወለጋ አይደለም ከማእከላዊ መንግስት የሚስተካከል ከምድር እስከ አየር ሀይል የታጠቀ ክልል ነው። ለሰላም ሁላችንም እንገዛ። በፍቅር በመከባበር አንድነታችንን እናስከብር። ታሪካዊ ጠላታችን ግብፅ እየሳቀች ነው። አንድ ካልሆንን በኤርትራ ደሴት ላይ ያስቀመጠቸው ዘመናይ ተዋጊ ሀይል እራሱ ቀላል ኢላማ መሆን ነው። መሪዋቻችን ከስካር ጡዘት ተላቀው መልካሙን የሚያስቡ በፀጋ የሸመገሉ ያድርግልን። All Ethio

አማርኛ ዜና 09-09-2012ዓ.ም

#አማርኛ_ዜና 09-09-2012ዓ.ም

Posted by Tigrai Mass Media Agency on Sunday, May 17, 2020
Facebook Comments Box
Spread the love